3. አንተን ተስፋ የሚያደርጉ፣ከቶ አያፍሩም፤ነገር ግን እንዲያው ያለ ምክንያት፣ተንኰለኞች የሆኑ ያፍራሉ።
4. እግዚአብሔር ሆይ፤ አካሄድህን እንዳውቅ አድርገኝ፤መንገድህንም አስተምረኝ።
5. አንተ አዳኜ፣ አምላኬም ነህና፣በእውነትህ ምራኝ፤ አስተምረኝም፤ቀኑን ሙሉ አንተን ተስፋ አድርጌአለሁ።
6. እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህንና ፍቅርህን አስብ፤እነዚህ ከጥንት የነበሩ ናቸውና።
7. የልጅነቴን ኀጢአት፣መተላለፌንም አታስብብኝ፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ እንደ ቸርነትህ ብዛት፣እንደ ምሕረትህም መጠን ዐስበኝ።
8. እግዚአብሔር መልካምና ቅን ነው፤ስለዚህ ኀጢአተኞችን በመንገድ ይመራቸዋል።
9. ዝቅ ያሉትን በፍትሕ ይመራቸዋል፤ለትሑታንም መንገዱን ያስተምራቸዋል።